facebook script

የስልክ ጥሪው

የስልክ ጥሪው — ሁሉም ተስፋ ያደረጉት እና የፈሩት ጥሪ ከጠዋቱ 2:00 ላይ መጣ: "ለያዕቆብ የሚሆን ልብ አለን" የሚል ድምጽ ከስልኩ ሌላኛው ጫፍ ተሰማ። ሁሉም ጥሪውን ተስፋ አድርገው ነበር፤ምክንያቱም የአስራ ሁለት አመቱ ያዕቆብ ለበርካታ ቀናት የልብ ንቅለ ተከላ ለማድረግ ከሚጠብቁት ሰዎች ዝርዝር ውስጥ አንዱ ነበር፤ሆኖም ብዙም ሳይቆይ ሁኔታው እያሽቆለቆለ ስለሄደ ለልብ ንቅለ ተከላ ጥሩ እጩ ተደርጎ እስከማይወሰድበት ደረጃ ደርሶ ነበር። ከዚያም የመጨረሻውን ተስፋ በመያዝ ስሙ ከዝርዝሩ ውስጥ ይሰረዝ ነበር፡፡
ነገር ግን በዚህ ቀን፣ ያዕቆብ እና ቤተሰቡ የማይታመን ስጦታ ሊቀበሉ ነው — ያም የአዲስ ልብ፤የአዲስ ህይወት ስጦታ ነው።

መጽሐፍ ቅዱስ ሁላችንም ከያዕቆብ የበለጠ ተስፋ አስቆራጭ ሁኔታ ውስጥ እንደምንገኝ ይነግረናል። ከዚህ በከፋ ህይወት አደጋ ላይ ነችና። የዘላለም ሞት አግኝቶናል፣ ምክንያቱም “የኃጢአት ደሞዝ ሞት ነውና” (ሮሜ 6፡23) ፣ “ሁላችንም ኃጢአትን ሠርተናል የእግዚአብሔርም ክብር ጎድሎናል” (ሮሜ 3፡23) ። በቀደመው ጥቅስ ውስጥ የሚገኘውን የመጀመሪያውን ቋንቋ ስንረዳ፣ ያለንበት ሁኔታ ምን ያህል ተስፋ አስቆራጭ እንደሆነ እንገነዘባለን። "ክብር ጎድሎናል" ተብሎ የተተረጎሙት ቃላቶች ቀጣዩን እርምጃን ያመለክታሉ — እንግዲህ ክብሩ እንደጎደለን እንኖራለን።

በመልካሙ ጊዜ ጥሩ ሰዎች ስለመሆናችን መናገር ቀላል ነው— ፍፁም ባንሆንም ክፉ ላንሆን እንችል ይሆናል። ይሁን እንጂ፤ጓደኛችን እኛ ተስፋ እናደርገው የነበረውን እድገት እና የደሞዝ ጭማሪ ሲያገኝ ወይም አዲስ መኪና ሲገዛ በልባችን ውስጥ ምቀኝነት ይፈጠራል። አንዲት የምታምር ሞዴል ወይም ተዋናይት ስንመለከት ልባችን በምኞት ይሞላል። እንዲሁም በመንገድ ላይ አንድ መኪና የትራፊክን ህግ በመጣስ ከፊት ለፊታችን ረድፍ ሳይጠብቅ አቋርጦ ሲገባ እስክንገረም ድረስ በከፍተኛ ንዴት እንቆጣለን። ሕይወታችንን በቅንነት በመረመርን መጠን ኃጢአተኛ ስለመሆናችን እንረዳለን።

እውነተኛ እይታ

በኦክስፎርድ ውስጥ አንድ ወጣት አምላክ የለሽ እና ፕሮፌሰር ራሱን በትኩረት ተመልክቶ ባገኘው ነገር ተገረመ። እንዲህም ሲል ጻፈ: - “በዚያ የሚያስደነግጠኝን ነገር አገኘሁ፤ የምኞት መካነ አራዊት፣ ያልተገደበ ፍላጎት ስፍራ፣ የፍርሃት ማቆያ፣ በሴቶች ላይ የሚደርስ ጭካኔ የተሞላው ወሲባዊ ጥቃት። ስሜ ሌጌዎን ይባል ነበር” (ሲ.ኤስ. ሉዊስ፣ በደስታ ተገረመ) ። የተነገረን ኃጢአት፣ ከኃጢአተኛ ልባችን ይመጣል። “በልብ ሞልቶ ከተረፈው አፉ ይናገራልና መልካም ሰው ከልብ መልካም መዝገብ መልካሙን ያወጣል፥ ክፉ ሰውም ከልብ ክፉ መዝገብ ክፉውን ያወጣል።” (ሉቃ 6:45) በእርግጥ፤ኃጢአተኛው ልባችን እውነተኛውን ኃጢአተኝነታችንን ከእኛ ይሰውራል፤ምክንያቱም “የሰው ልብ ከሁሉ ይልቅ ተንኰለኛ እጅግም ክፉ ነው፤”(ኤር.17፡9):

እንደ ያዕቆብ የችግራችን ምንጭ ልባችን ሆኖ እናገኘዋለን። ፈውስ አናገኝም። ምንም ዓይነት ሕክምና ወይም እርዳታ አያድነንም፡፡ ችግር ያለበት ልባችን መተካት አለበት፤አለበለዚያ እንሞታለን። ያዕቆብ ስሙን ዝርዝር ውስጥ አስቀምጦ መጠበቅ ነበረበት። ምንም ያህል ገንዘብ የሚፈልገውን ሊገዛለት አይችልምና። ልብ የሚሰጠው ባይኖር ደግሞ ይሞታል።
የኛም ሁኔታ ተመሳሳይ ነው፣ ነገር ግን መጽሐፍ ቅዱስ በዚህ ተስፋ አስቆራጭ ሁኔታ ውስጥ ላለን ሁሉ የምስራች ዜና አለው። “አዲስም ልብ እሰጣችኋለሁ አዲስም መንፈስ በውስጣችሁ አኖራለሁ፤ የድንጋዩንም ልብ ከሥጋችሁ አወጣለሁ የሥጋንም ልብ እሰጣችኋለሁ።” በማለት እንዲህ ያለ ስጦታ እንዳለ ያረጋግጥልናል (ሕዝቅኤል 36፡26) ።
እጅግ የላቀ ቢሆንም፣እስኪደርሰን ወረፋ እየጠበቅን አንቆይም። ይህ ምትክ ልብ ወዲያውኑ ይገኛል፡፡ አንድ ጊዜ የራሳችንን ልብ ካገኘን፣ መኖርን ብቻ ሳይሆን የላቀ ጥራት ያለው ሕይወትም እንኖራለን።

የያዕቆብ ቤተሰብ የስልክ ጥሪው ያስፈራው ነበር፤ምክንያቱም አሰራሩ ከባድ አደጋዎችን ያስከትላልና። ጤናማ ልብ ከመተከሉ በፊት የታመመው የያዕቆብ ልብ መወገድ ነበረበት። ቀዶ ጥገናው ከተጀመረ በኋላ፤ወደ ኋላ መመለስ አይኖርም:: ወላጆቹ እነዚህን ሁሉ ሃሳቦች በአዕምሮአቸው ውስጥ ይዘው ምሽቱን አሳለፉ፡፡ ከዚያም ራሳቸውን እና ያዕቆብን ወደ ሆስፒታል ለሚደረገው የእጣ ፈንታ ጉዞ አዘጋጁ። እዚያም እንደደረሱ ልጃቸው በሆስፒታል አልጋ ሲሄድ ተመለከቱ።

እኛም በተመሳሳይ ሁኔታ ውስጥ ማለፍ አለብን። ያዕቆብ ከቀዶ ጥገናው በፊት ሐኪሞቹ የራሱን ልብ እንዲያስወግዱ መፍቀድ እንደነበረበት ሁሉ፤እኛም አሮጌውን ልባችንን መተው አለብን። ፈውስ ከማያመጣ የይስሙላ አካሄድ፣ከጥቃቅን ማስተካከያ ወይም እርማት በላይ እንደሚያስፈልገን መገንዘብ አለብን። የተሟላ ቀዶ ጥገና ያስፈልገናል:: ከዚያ ያነሰ ምንም አይጠቅመንምና።

ውድ ስጦታ

ይህ አስፈሪ አደጋ ያዕቆብን እና ወላጆቹን “ልብ ተገኝቷል” የሚለውን የስልክ ጥሪ እንዲፈሩ የሚያደርግ አንድ ምክንያት ነበር። የያዕቆብ ወላጆች ለልጃቸው የተሻለ ሕይወት በማግኘታቸው ተደስተው የነበረ ቢሆንም፣ ሆኖም ሌላ ይበልጥ አሳሳቢ የሆነ እውነታን ተጋፍጠዋል።
አዲስ ተስፋ የሰጣቸው ያው ክስተት የሌላ ቤተሰብን ተስፋ እንዳጨለመ ተረድተዋል። የያዕቆብ የሕይወት ዕድል በሌላ ሰው ሞት ምክንያት የመጣ ነውና።

ለመንፈሳዊ ልብ ንቅለ ተከላ፣ከኃጢአት ለመዳን፣ በዚህ እና አሁን ለሚኖረን የተሻለ ሕይወት እንዲሁም ከዚህም በኋላ የዘላለም ሕይወት ለማግኘት ያለን ዕድል የመጣው በተከፈለ የሕይወት ዋጋ ነው። "ነገር ግን ገና ኃጢአተኞች ሳለን ክርስቶስ ስለ እኛ ሞቶአልና እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን የራሱን ፍቅር ያስረዳል።" (ሮሜ 5፡8) ። አስተውሉ፣ ክርስቶስ የሞተልን “የተገባን ስለሆንን፣” ወይም “የእግዚአብሔርን ሕግ ፍጹም በሆነ መንገድ ስለታዘዝን” ወይም “የሚያስፈልገንን ጠንቅቀን ስላወቅን” ሳይሆን “ገና ኃጢአተኞች ሳለን” ነው።

የያዕቆብ ልብ ያለ ንቅለ ተከላ እየከፋ የሚሄድ ነው። እጅግ የሚያስፈልገው በመሆኑ የሚገባው አድርጎታል። ስለሆነም ጤናማ ልብ እንዲሰጠው በአንድ ሰው እና ስፍራ ላይ ለመደገፍ ተገደደ፡፡ ልብ በምንም አይነት ዋጋ ሊገዛ አልችልም፤በገንዘብ የሚገኝ ቢሆን እንኳን፤እሱ እና ቤተሰቡ አንዱንም መግዛት አይችሉም ነበር:: እንዲሁም ደህንነት የሚገኘው በተመሳሳይ እውነት ነው፡- “የኃጢአት ደመወዝ ሞት ነውና፤ የእግዚአብሔር የጸጋ ስጦታ ግን በክርስቶስ ኢየሱስ በጌታችን የዘላለም ሕይወት ነው።” (ሮሜ 6፡23) ። ስለዚህ የዘለዓለም ሞት እንዳገኘን ያስጠነቀቀን ያው ጥቅስ መድኃኒቱንም በስጦታ ሲያበስር እናገኘዋለን።

ፈጣን አቅርቦት

ይህ ከሁሉ የላቀው አዲስ ልብ እና በዘላለም ውስጥ እጅግ ዋጋ ያለው ስጦታ የእርስዎ ሊሆን ይችላል። የወረፋ ዝርዝር ውስጥ መግባት አያስፈልግዎትም። መጠበቅ አይኖርብዎትም። በቀላሉ በመጠየቅ እዚህ እና አሁን ሊያገኙት ይችላሉ። አስፈላጊ እውነታዎችን ተመልክተዋል።
በቀላሉ የሚያስፈልግዎትን ይወቁ፣ ይህ አዲስ ልብ እንደሚያስፈልገዎት ይናገሩ፣ከዚያም እግዚአብሔር እንዲሰጥዎት ጠይቁ። ምንም የአስማት ቀመር የለውም፤ የተቀመጡ ውሱን ቃላት የሉም:: ዝም ብለው ይጠይቁ፡፡

ያዕቆብ የንቅለ ተከላውን በከፍተኛ መንፈስ አከናወነ። አዲስ ልብ ብቻ ሳይሆን አዲስ ሕይወትም አገኘ። ዳሩ ግን ያንን አዲስ ሕይወት እንዴት እንደሚኖር መማር ነበረበት። አዲሱን ልብዎን ሲቀበሉ፣አዲሱን ህይወት እንዴት እንደሚኖሩ መማር ያስፈልግዎታል።
አዲሱን ሕይወት ትመሩ ዘንድ እንዲረዳችሁ፣እግዚአብሔር ቤተክርስቲያንን፤እና አዲስ ልብ የተቀበሉ ሌሎች ህብረቶችን አዘጋጅቶላችኋል። በስጦታው ይደሰቱ!

––––––––––

*ስሙ ተቀይሯል፡፡
ጥቅሱ የተወሰደው ከመደበኛው ትርጉም ነው፡፡ መብት ሁሉ የተጠበቀ ነው © 1982 by Thomas Nelson, Inc. የተፈቀደ፡፡ መብት ሁሉ የተጠበቀ ነው፡፡